Global Peace Federation- Ethiopia

Non Government and Profit Organization.

The government is attempting to strengthen, peace, friendship and alliance among its people and is making significant efforts to this end. But, peace, friendship and alliance is not created at the required level. People are noticed to have lost their values and traditions and conflicts to related to religion, language, ethnicity and politics are rampant. Displacement, suffering and assassinations along with property destructions are noticed following this conflicts. Thus, global – peace federation- Ethiopia is working alongside stockholder bodies to promote, peace, friendship alliance in Ethiopia and make its own contribution after obtaining a legal business license registered before the civil societies agency according to the Ethiopian law.


ግሎባል ፒስ ፌደሬሽን-ኢትዮጲያ መንግስታዊ ያልሆነ፣ለትርፍ ያለተቛቛመ ድርጅት ነዉ(Non-Governmental & Non-Profit Organization)


መንግስት በሀገራችን ኢትዮጵያ በሕዝቦች መካከል ሰላም፣ ወንድማማችነትና ወዳጅነት እንዲጠናከር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ይሁንና በሚፈለገውና በሚታሰበው ልክ ሁሉም ቦታ ሰላም፣ወንድማማችነትና ወዳጅነት ሰፍኖ አይገኝም፡፡ በአንድ አንድ ቦታ ላይ እሴቶቻችን ተሸርሸረዉ አልፎ አልፎ እዚህም እዚያም ሰዎች በእምነት፣በቋንቋ፣ በብሔር፣በፖለቲካ አመለካከትና አስተሳሰባቸው ሲጋጩ፤ግጭቱንም ተከትሎ መፈናቀል ግድያ እና እንግልት እንዲሁም የንብረት ውድመቶች ሲከሰት ታይተዋል፡፡ በመሆኑም ግሎባል ፒስ ፌዴሬሽን- ኢትዮጵያ/Global Peace Federation-Ethiopia)እነዚህ ግጭቶችና አለመግባባቶች በሚፈቱበትና ሰላም፣ ወንድማማችነትና ወዳጀነት በሀገራችን በሚሰፍንበት መፍትሄ ዙርያ ከባለ ድርሻ ካላት ጋር ለመስራት (አስተዋጽኦ ለማድረግ) በኢትዮጵያ ህግ በሲቪል ማህበራት ኤጄንሲ ተመዝግቦ ህጋዊ የስራ ፍቃድ ተሰጥቶት እየሰራ ይገኛል፡፡

ዋና ዋና ዓላማዎቹም፡-

1.ሰላም፣ወዳጅነትና ወንድማማችነት በሕዝቦች መካከል እንዲጠናከር መንግስት ከሚያደርገው ጥረት ጐን ለጐን ከእምነትና የትምህርት ተቋማት፣የሙያ ማህበራት፣ የወጣቶች የሴቶች፣የአካል ጉዳተኞች፣ የፖለቲካና የሲቪል ማህበራት እንዲሁም ከግለሰቦችና ቡድኖች ጋር በመተባበር ሰላም፣ወንድማማችነት እና ወዳጅነት በግለሰቦች፣በቤተሰብ፣ በእምነቶች፣በማህበረሰብና በህዝቦች መካከል እንዲጎለብት ውይይቶችን በማዘጋጀት ችግሮች እንዳይፈጠሩ ከተፈጠሩመ በአስቸኳይ እንዲፈቱ መስራት፡፡
2.ሰው በማንነቱ፣በብሔ፣በቋንቋውና በቆዳ ቀለሙ ልዩነት፣በእምነቱና በፖለቲካ አመለካከቱ እንዳይጠላ፣እንዳይጎዳ፣እንዳይገለልና የግጭት መነሻም እንዳይሆን የሚያስተምሩ፣ እያዝናኑ ግንዛቤ የሚያስጨበጡ፤የሙዚቃ ኮንሰርቶችን፣የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያሳትፉ የስፖርትና የባህል ፌስቲቫሎችን፣ወርክሾፖችን ፣እያዝናኑ የሚያስተምሩ የጥያቄና መልስ ወድድሮችን፣ኮንፍረንስ፣የኪነጥበብና የስነጥበብ ዝግጅቶችን ማካሄድ፡፡
3.ስለ ሰላም፣ወንድማማችነትና ወዳጅነት የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ የሚቀሰምበት መድረኮችን በመፍጠር፣ለህዝባችን በሚጠቅም መልኩ በሚዲያ፣በህትመትና በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ተደራሽ ማድረግ፡፡
4.ሀገር በቀል ባህላዊና ሀይማኖታዊ የግጭ አፈታት ዘዴዎችን በማጎልበት በእነት፣ በብሔርና በፖለቲካ ልዩነት በግለሰቦች፣ በህብረተሰብና በአካባቢዎች መካከል ግጭትና ቂም በቀል እንዳይኖር መስራት፡፡
ስለ ሰላም፣ እኩልነት፣ ወንድማማችነትና ወዳጅነት ተምሳሌታዊ ስራ የሰሩትን የእምነት አባቶች፣ የኪነ ጠበብ እና ሥነ ጥበብ ባለሙያዎችን፣ግለሰቦች፣ ቡድኖችና ድርጅቶችን መድረኮች ላይ በመጋበዝ እውቅናና ሽልማት መስጠት፣የድርጅቱ የሰላምና የክብር አምባሳደር አድርጎ መሾምና ሌሎችም የነሱን አርዓያ ተከትለው ስለ ሰላም፣ ወንድማማችነት እና ወዳጅነት መጎልበት የድርሻቸውን እንዲወጡ ማነቃቃት፣ማሳተፍና ሌሎች ስለ ሰላም መጎልበት ስተዋጽዖ ላቸዉን ተገባራቶች መከወን፡፡

ራዕይ፡-

በኢትዮጵያ፣በአፈሪካ ብሎም በአለም ወዳጅነትና ወንድማማችነት ተጠናክሮ ሰላም የሰፈነባት አለም ማየት፣
ሰዉ በእምነቱ፣በባህሉ፣በቛንቛዉ፣በእመነቱና በፖለቲካ አመለካከቱ ሳይሆን በስራዉ ብቻ የሚመዘንበት ምቹ አለም መፍጠር፡፡